ማህበሩ ከዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ የስልጠና እና ልማት ባለሙያዎች ማህበር ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት ጋር በትብብር ለመስራት ሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በካሶፒያ ሆቴል ተወያየ፡፡ በውይይቱ የማህበሩን ይፋዊ ድረ-ገጽ እና ዋና ዋና ስራዎችን ፕሬዝዳንቱ አቶ ምስጋናው ጌትነት ያስተዋወቁ ሲሆን ማህበሩ በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ የውስጥ አሰራር መመሪያዎቹን በማዘጋጀት፣ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በጋራ የመስራት ስምምነት እንደፈጸመ አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል በስልጠና እና ልማት ዘርፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence/AI) የሚያሳድረውን አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖን በተመለከተ አቶ ብሩክ ታደሰ በፊንላንድ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የመወያያ ጽኁፍ አቅርበዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ተሳታፊዎች በሀገራችን ከ328 በላይ ማህበራት ቢኖሩም በተገቢው የተቋቋሙበትን ዓላማ በመፈጸም የሚገኙት ጥቂቶች መሆናቸው ተገልጾ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ የሆነው የኢትዮጵያ የስልጠና እና ልማት ባለሙያዎች ማህበር ትምህርት መውሰድ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡  

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

WhatsApp
Telegram
Scroll to Top