የሙያ ማህበራት ተጽእኖ በኢትዮጵያ፡ ተሞክሮና ችግሮች ጥናታዊ ጽሁፍ ለውይይት ቀረበ

የኢትዮጵያ የስልጠና እና ልማት ባለሙያዎች ማህበር ከኤም ጂ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር የሙያ ማህበራት ተጽእኖ በኢትዮጵያ፡ ተሞክሮና ችግሮች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናት ለምሁራን፣ ለተለያዩ የሙያ ማህበራት ኃላፊዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለውይይት ቀረበ፡፡

የጥናቱ ዋና ዓላማ ለሙያ ማህበራት ጥንካሬ፣ ለፖሊሲ አውጭዎች እናዲሁም በሙያ ማህበራት ዘርፍ ላይ በመሰማራት በጎ ተጽእኖ ለመፍጠር ለሚያልሙ ገንቢ ምክረ-ሃሳብ ለማካፈል መሆኑን የጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢ የኢትዮጵያ የስልጠና እና ልማት ባለሙያዎች ማህበር መስራችና ፕሬዝዳንት ምስጋናው ጌትነት ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ የሙያ ማህበራት የተቋቋሙበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ልምምድ የሌላቸውና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን የገለጹት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ የሙያ ማህበራትን መሠረት ያደረጉ ተመሳሳይ ጥናቶች ሊበራከቱ እንደሚገባ በአውደ ጥናቱ ማሳረጊያ ገልጸዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

WhatsApp
Telegram
Scroll to Top